የኢትዮጵያዊ ተባባሪዎቻችንን የሙዚቃ መሳሪያዎች መተካት
Ethiopia
- Caregivers
- Mental health
- Adults
- Activities
ያለፈው ዓመት የምክር ኮሚቴ አባሎቻችን Erin Williams-Jones እና Alastair Robertson በኢትዮጵያ የሚገኙትን ተባባሪዎቻችንን የክትትል ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎቻቸውን ማየት ችለው ነበር። ተጨማሪ መሳሪያ የሚያስፈልጋቸው ተባባሪዎችንም መለየት ችለው ነበር። Erin እና Alastair በቅርብ የጻፉት ብሎግ ላይም ትዝ ይላችሁ እንደሆን፣ ለቤዛ ሳይኪያትሪክ ክሊኒክ አንድ የተበላሸ ቦንጎ መሳሪያን አድሰናል።
የተበላሹ የሙዚቃ መሳሪያዎች ሁሉ በቀላሉ ሊታደሱ እንደማይችሉ እንረዳለን፤ በልማት ላይ ያሉ የሙዚቃ ፕሮግራሞች ላይም የመሳሪያ እጥረት ሊከሰት እንደሚችልም እንረዳለን። የኢትዮጵያዊ ተባባሪዎቻችንን የሙዚቃ መሳሪያዎች በመተካት ይበልጥ ልንረዳቸው እንደምንችል ተገንዝበን፣ ማክዳ ወደ ኢትዮጵያ በጉጓዘችበት ጊዜም ይህንን እርዳታ ዕውን አድርገናል።
ለለቤዛ ሳይኪያትሪክ ክሊኒክ እንዲሁም ለገፈርሳ የአዕምሮ ጤና ማዕከል ሁለት ከበሮ ማስረከብ ችለን፣ እነዚህ መሳሪያዎች የአቋሞቹን ሰራተኞች ከ226 የአዕምሮ ታማሚዎች ጋር የሚሰሩትን የሙዚቃ ፕሮግራም እንዲቀጥል ይረዳል ብለን ትስፋ እናደርጋለን።
እርሶ በኢትዮጵያ የሚገኙ እና ሙዚቃን በሚሰጡት የህክምና እንክብካቤ አገልግሎት ላይ የመጠቀም ፍላጎት ያሎት ባለሙያ ኖት?
በመጀመሪያው ክፍል በተላያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች ድምፅ ማውጣትን ተምርያለሁ። ጥሩ ድምፅን ማውጣት እንደምችልም ተገንዝብያለሁ።
የFENAID ስልጠና ተሳታፊ፣ ኢትዮጵያ 2024
በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሆነ እና በአዕምሮ ጤና እንክብካቤ ላይ ሙዚቃን ስለመጠቀም የመማር ፍላጎት ካላችሁ የአለምአቀፍ ብሮግራም አስተባባሪያችንን ማክዳ ሚሼልንድጋፍ እንዴት እንደምናደርግላችሁ ለተጨማሪ መረጃ በኢሜል makedamitchell@musicastherapy.org ማነጋገር ትችላላችሁ፡፡