ትብብርን ማጠናከር በኢትዮጵያ፡ የአዲስ አበባ አጋሮቻችን ጉብኝት
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Children
- Disability
- Mental health
- Awareness
- Activities
- Tailored Training (On-site)

በገና ወቅት፣ እኔ (ሄንሪ) ከዓለም አቀፍ ፕሮግራም ስራ አስኪያጅ ማክዳ ጋር በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ የሚገኙ ሦስት የMusic as Therapy International አጋሮችን የመጎብኘት እድል ነበረኝ።
በቆይታችንም ሆስፒስ ኢትዮጵያ፣ FENAID (Fikir Ethiopian National Association for Intellectual Disabilities)፣ እና ቤዛ የስነ አዕምሮ ክሊኒክ ከሚባሉት አጋሮቻችን ጋር የሚሰሩ ባለሙያዎችን አናግረን ነበር። ዓላማችን አሁን የሚያዘጋጁትን የሙዚቃ ስርዓት እና ልምምድ፣ የሚሹትን የዘላቂ ድጋፍ ዓይነት እና ከMusic as Therapy International የተጨማሪ የሙዚቃ ስልጠና ፍላጎታቸውን ይበልጥ ለመረዳት ነበር።
በመስከረም ወር ያሳተምነውን የኢትዮጵያ ጋዜጣችንን ተጽእኖ ምለካትም ፈልገን ነበር። እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ጋዜጣው እንደ ፍላጎታችን እንዳልተሰራጨ ተረድተናል። ነገር ግን አጋሮቻችን ጋዜጣውን እንደገና እንድናካፍልላቸው በመጠየቃቸው ደስ ብሎናል።
በጉብኝታችን ታታሪ እና ቁርጠኛ፣ በስራቸው ላይ አተኩረው የሚሰሩ ባለሙያዎችን ማግኘታችን ለእኔ እጅግ በጣም አዎንታዊ ነበር።ለስራቸው ያላቸውን ፍቅር እና የስራቸውን ተፅእኖ ማየት በእውነት አበረታች ነበር። አጋርነታችንም አጠናክረን እንድንቀጥል አጓግቶናል።
ሆስፒስ ኢትዮጵያ
ሆስፒስ ኢትዮጵያን ስንጎበኝ ከወንጌል ጋር ተገናኝተን ነበር። እሷም ባለፈው ዓመት ወስጥ ሆስፒሱ ስላሳካው እድገት በታላቅ ኩራት ነግራናለች። የህይወት ፍጻሜ ፈተና ለሚገጥማቸው ህጻናት አዲስ ፕሮግራም ለመመስረት ያላቸውን እቅድም አጋርታናለች። ይህ እቅድ ከአዋቂዎች አልፎ ለህጻናት እንክብካቤ ሙዚቃን መጠቀም እንዴት ሊለይ እንደሚችል እንድንወያይበት አድርጎን ነበር።
በእንክብካቤ ስራዓታቸው ላይ ሙዚቃ ምን ያህል እንደተዋሃደ መስማት አበረታች ነበር፣ እና ወደ የህፃናት ህክምና ማስታገሻ እና እንክብካቤ ስልጡን ለማስፋፋት ያለው ሰፊ እድልም ግልፅ ነበር። ሙዚቃ በአዲስ እና ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ስራቸውን እንዴት መደገፍ እንደሚችልም ብጉብኝታችን ተገንዝበን ነበር፤እንደሚቀጥልም ተስፋ እናደርጋለን።
FENAID
በሁለተኛው ቀናችን፣ FENAIDን ጎበኘን። እንዴት ያለ ድንቅ ቦታ እንደሆነም አየን። ባለሙያዎቻቸው ሞቅ ያለ አቅባበል አድርገውልን አስደናቂ ቤታቸውን አሳይተውን ነበር። FENAID የመማር እክል ያለባቸው ወጣቶች የሚማሩበት፣ ችሎታቸውን የሚያዳብሩበት እና የጠንካራ ማህበረሰብ አካል ሊሆኑበት የሚያስችል እንክብካቤን ይሰጣል።
ምንም እንኳን በጉብኝታችን ወቅት የሙዚቃ ክፍለ ጊዜን ለመመስከር ባንችልም ከደመቁ የመማሪያ ክፍሎች ፣ሞቅ ያሉ የጨርቃጨርቅ ስራ ክፍሎች እና ባለሙያዎች እና ተጠቃሚዎች ካካፈሏቸው ታሪኮች ሙዚቃ ምን ያህል አስፈላጊ እና ጠቃሚ እንደሆነላቸው ለማየት ግልፅ ነበር።
ከባለሙያዎች ጋር ባደረግነው ውይይት መንግስት እና ሰፊው የት/ቤቶች ኔትወርክ ሙዚቃ በትምህርት ላይ ያለውን ሚና እንዲዳስሱ ለማድረግ በሚሰሩት ስራ ላይ ከእኛ የበለጠ ዘላቂ ድጋፍ እንደሚፈልጉም ተገንዝበናል።
ለቤዛ የስነ አዕምሮ ክሊኒክ
ለዛ ቡና በሚባል ቤት ግሩም ፍርፍር እና እስፕሪስ ጁስ ከጠጣን በኋልም የሞላው ሆዳችንን ይዘን ወደ ለቤዛ የስነ አዕምሮ ክሊኒክ አመራን።
እዛም ወንድወሰን ተቀብሎን ከክሊኒክ ባለሙያዎቻቸው ጋር በአዕምሮ ህክምና ላይ ሙዚቃን እንዴት እንደሚጠቀሙ ተወያይተንበታል። ሙዚቃ ለታካሚዎቻቸው ጠቃሚ እንደሆነ እና በህክምናው ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ግልፅ ነበር።ነገር ግን ማንኛውም የህክምና ቦታ እንደሚገጥመው እዚህም የሰራተኞች መልቀቅ እና ሽግግር ችግር ለወደፊቱ የሙዚዋ ክፍለ ጊዜዎች ፈተና ሊሆን እንደሚችል ገልፀውልናል።እንድ ባለሙያ ለሌሎች እውቀቱን እና ክህሎቱን እንዲያካፍል በመደገፍ ለዚህ ፈተና መፍትሄ ሊሆን እንደሚችልም ተወያይተንበታል።
ጉብኝታችን ሙዚቃ በእንክብካቤ ላይ ያለውን ጥቅም እና ዋጋ እንደገና እንድንገነዘብ ርድቶናል፣ ባለሙያዎች
ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በኢትዮጵያ ወስጥ ተጋላጭ ሁኔታ ላይ ላሉ ሰዎች ለመርዳት ምን ያህል ድጋፍ እና ጥረት እንደሚያደርጉም አይተናል።እንዲሁም ሙዚቃ በእንክብካቤ ላይ ያለውን ሚና ሰው የበለጠ እንዲገነዘበው ለማድረግ ከእኛ የሚጠበቀውን ድጋፍ ለመመልከት ጠቃሚ ግንዛቤን ሰጥቶናል።ያለውን ጥረት እና ስራ በማየታችን እጅግ በጣም ደስ ብሎናል፣ወደፊትም ሙዚቃ የጠነከረ የእንክብካቤ አካል ሆኖ እንዲቆይ ለማድረግ አዳዲስ መንገዶችን ለመዳሰስ ጓጉተናል።
~ ሄንሪ (Henry)
በኢትዮጵያ የሚገኙ ከሆነ እና በአዕምሮ ጤና እንክብካቤ ላይ ሙዚቃን ስለመጠቀም የመማር ፍላጎት ካላችሁ የአለምአቀፍ ብሮግራም አስተባባሪያችንን ማክዳ ሚሼልንድጋፍ እንዴት እንደምናደርግላችሁ ለተጨማሪ መረጃ በኢሜል makedamitchell@musicastherapy.org ማነጋገር ትችላላችሁ፡፡
በአዲስ አበባ እና በሌላም ቦታ ላይ የሙዚቃ ቴራፒ እየተጠቀሙ ያሉ አጋሮቻችን ስላሳለፉት ጉዞ፣ ፈተና እና ስኬቶች ያንብቡ።
Related projects
-
Support Visit: Hospice Ethiopia, FENAID and Lebeza Psychiatry Clinic (Addis Ababa) 2025
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Disability
- Mental health
- Young people
-
Partner Newsletter: Ethiopia 2024
Ethiopia
- Adults
- Caregivers
- Disability
- Elderly
- Mental health
- Young people